የቶሮንቶ የሕዝብ ቤተመፃሕፍት ብዙ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በነፃ ይሰጣል። በከተማችን አዲስ የሆኑ ሁሉ እንዲቋቋሙ እንረዳለን።
ጎብኙን እና
- የላይብረሪ ካርድ በነፃ ይውሰዱ; ካርዱን ለመውሰድ ሁለት ስምና አድራሻ ያላቸው መታወቂያዎች ያስፈልጋሉ
- በኮምፒዩተራችን ይጠቀሙ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቅርንጫፍ ቤተመጻሕፍት ይገኛሉ፤ ኢንተርኔት፤ወርድና ዳታ የመሳሰሉ የተሟሉ አገልግሎቶች አሉ
- የነፃ wifi በሁሉም ቅርንጫፍ ቤተመፃሕፍት መጠቀም ይቻላል
- መፃሕፍት፤ ቪድዎች ሌላም በግል ለመዋስ ወይንም በኢሜል ለመዋስ በአርባ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ይገኛሉ።
- ለማቋቋም የተመደቡ ሠራተኞች፤ ሥራ ለመፈለግ፤መንጃ ፈቃድ ለማውጣት እና ሌላም ብዙ ጉዳዮች ይረዳሉ
- የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለመማርና ለመለማመድ በትምሕርት ይሣተፉ
- በኤለክትሮኒክ የተከማቹ ለዓዋቂና ለልጆች የእንግሊዝኛን ትምህርት ይጨምራል። ዳውንሎድ ማድረግም ይቻላል
- ወደ ፕሮግራማችን ይምጡ ብዙ ክፍሎች አሉ ፤አዲስ አነስ ያለ ንግድ ለመጀመር፤የልጆች ተረት መንገር፤ ሥራ መፈለግ
- በመቶ የሚቆጠሩ ቅርንጫፍ ቤተመፃሕፍት የሚገኝትን ሠራተኞች ይተዋወቁ ጥያቄያችሁን ሁሉ እንቀበልና ወደሚመለከተው ሰው እናስተላልፋለን። በተለያዩ ቋንቋዎች ኣስተርጓሚዎች እናቀርባለን።
በቶሮንቶ ቤተመፃሕፍት ባለነው በሁላችን ሥም በቅርብ እንድናያችሁና ዝግጅቱን እንድትካፈሉ መልካም ዕድል እንመኛለን።